ነዳጅ ወደ ኮንትሮባንድ አከባቢ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ ተያዘ።
ታህሳስ 29 ቀን 2017 ዓ.ም (ነ.ኢ.ባ) በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የተወሰነ ሲሆን አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር አንድ ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ መወሰኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። |