የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን መ/ቤት ሠራተኞች አዲስ ዓለምአቀፍ የኢግዚብሽን እና ስብሰባ ማዕከልን ጎበኙ።
መጋቢት 1/2017 አዲስ ዓለምአቀፍ ኢግዚቢሽንና ስብሠባ ማዕከልን የባለስልጣን መ/ቤቱ የበላይ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጎበኙ፡፡ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል፣የስብሰባና ኤግዚብሽን ማዕከልን ያካተተው ማዕከሉ ዓለምአቀፍ ስብሰባዎችን፣የንግድ እና የኪነጥበብ ኢግዚብሽን ማካሄድ የሚያስችል እንደሆነ የማዕከሉ አስጎቢኚ በኩል ገለጻ ተደርጓል፡፡ በሀገራችን መስል ማዕከላት መኖራቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ተሳታፊ ከመሆን ጋር በተያያዘ ጥሩ ዕድሎችን ይዞ የሚመጣ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡ |