በመስከርም 2017 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ።
ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ/ም
በመስከርም 2017 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ከግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ ከብሔራዊ ግሪድ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ጋር ተያይዞ የዘርፉን የፋይናንስ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ በተለይም የዉጭ ምንዛሪ ሪፎርሙ እና የዋጋ ንረትን ታሳቢ በማድረግ የቀረበ የፋይናንስ ዘላቂነት ጥናት አሁን ሥራ ላይ ያለዉ ታሪፍ በኃይል አቅራቢ ተቋማት ላይ የተወሰነ የገቢ ፍላጎት ጉድለት እንደሚያመጣ ይጠበቃል። ስለሆነም መንግስት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታርፍ ምንም አይነት የዋጋ ንረት እንዳያስከትል እና ህብረተሰቡ ላይ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫና ሳይፈጥር የዘርፉን የፋይናስ አቋም ለማሻሻል ባለው ቁርጠኛ አቋም ቀደም ሲል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከተለያዩ አገሮችና መልቲላተራል ተቋማት የተወሰደውን ብድር በመልሶ ማበደር ስምምነት መሠረት ብድሩ ወደ ካፒታል እንዲዞርላቸዉ ወስኗል። የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣንም የሁለቱንም ተቋማት የፋይናንስ ሰነድ በዝርዝር በማየት የታሪፍ ማስተካከያ ማድረግ እንደማያስፈልጋቸው ያመነበት በመሆኑ በመስከረም 2017 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ሳያስፈልገው ከግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እንዲቀጥል ወስኗል።
|
- Hits: 1984