የሀገርን ጥቅም በማስቀደም ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር

 

የሀገርን ጥቅም በማስቀደም ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር

ሀገራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያ ቁመና በሚል ርዕስ በወቅታዊና ሀገራዊ ቀዳሚ አጀንዳ ላይ የተቋሙ ሠራተኞች ውይይት አደረጉ፡፡

ውይይቱን በንግግር ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) አፅኖት ሰጥተው እንደገለጹት ከየትኛውም የውስጥ አጀንዳችን በላይ በብሔራዊ አንድነታችን እና ጥቅማችን ዙሪያ የጋራ እና የጸና አቋም ሊኖረን ይገባል ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ሠራተኞችም ብሔራዊ አንድነትን ማስቀደምና የመጡ ለውጦችን ለማስቀጠል ተቋማዊ አሰራሮችን ማሻሻል እንደሚያስፈልግና በኢትዮጵያ አንድነትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አንድ አቋም መያዝ እንዳለበት የጋራ አቋማቸውን ገልፀዋል፡፡