መንግስት የነዳጅ ሪፎርም ስራን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ከ2014 በጀት አመት አንስቶ በሪፎርም ስራው በርካታ ውጤቶች ተመዝግቧል፤

 

 
  • መንግስት የነዳጅ ሪፎርም ስራን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ከ2014 በጀት አመት አንስቶ በሪፎርም ስራው በርካታ ውጤቶች ተመዝግቧል፤
  • በተደረገው የዋጋ ማስተካከያ እርምጃ ቀደም ባሉት ዓመታት በየወሩ በአማካይ እስከ ብር 10 ቢሊዮን ሲመዘገብ የነበረው ከፍተኛ ዕዳ (ተሰብሳቢ ሒሳብ) ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቆም እና ከጥቅል ድጎማ ሙሉ በሙሉ መውጣት ተችሏል።
  • በ2016 በጀት ዓመት ከሞላ ጎደል ያለ ምንም ጥቅል ድጎማ እንዲቀርብ ከመደረጉም በተጨማሪ የነበረውን ተሰብሳቢ ዕዳ በከፍተኛ መጠን ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡
  • በ2017 በጀት ዓመት የተከናወነውን አገርአቀፍ ማክሮኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ትግበራን ተከትሎ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ በመጨመሩ ከፍተኛ መጠን ያለው ድጎማ በማድረግ የዋጋ መረጋጋት መፍጠር ተችሏል ፤

v በሂደትም ተጠቃሚውን በማይጎዳ መንገድ ቀስ በቀስ ከድጎማ ለመውጣት የሚያስችል የዋጋ ግንባታ በማድረግ የተሰብሳቢ ሂሳብ ጭማሪው በነበረው የጭማሬ ፍጥነት እንዳይቀጥል ተደርጓል።

Ø ነገር ግን የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ የነበሩ ችግሮች አሁንም ድረስ ሳይፈቱ፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች እየተፈጠሩ ዘርፉን ውስብስብ እያደረጉት ይገኛል፤

Ø የነዳጅ ግብይቱን ላይ ያለው ግልፅ ህገ-ወጥነት እና ሌብነት እየሰፋ በመምጣቱ የችግሩን ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር ጥናት ተደርጓል፤

በጥናቱ የተለዩ ችግሮች፡-

- በህገ ወጥ መንገድ በመሸጥ የሚገኘው ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑ

- የነዳጅ ኩባንያና ማደያ ያልተገባ ጥቅም መፈለግ እና ሃላፊነትን አለመወጣት

- በሁሉም የተቆጣጣሪ አካላት የሚስተዋል ስነምግባር ጉድለት፥ አቅም ማነስ

- በስራ ላይ ያለው የገበያ ድርሻ አሰራር ችግር

- አቅርቦቱ ተገማች አለመሆን በየጊዜው መቆራረጥ የቁጥጥርና ክትትል ስራው በቴክኖሎጂ የተደገፈ አለመሆን

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች

- ሕገወጥነትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የሕግ ማእቀፎችን ወደ ስራ ማስገባት

- በግብይት ሰንሰለቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን ማድረግ እና ሕጋዊ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ

- የቀጥታ ተጠቃሚ ድርጅቶችን የነዳጅ አጠቃቀም ጥናት ማድረግና ጥናቱ በተገኙ ግኝቶች መሠረት ማስተካከያ ሥራዎች የተሰሩ መሆናቸው

- በሕገወጥ ሥራ ላይ ተሰማርተው የተገኙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እና

- የአቅርቦት ስርዓቱ ግልጸኝነት እንዲኖረውና የቁጥጥር ሥራዎችን ማቅለል የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በማስለማት ወደ ስራ እኒዲገቡ ማድረግ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡