መንግስት የነዳጅ ሪፎርም ስራን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ከ2014 በጀት አመት አንስቶ በሪፎርም ስራው በርካታ ውጤቶች ተመዝግቧል፤
v በሂደትም ተጠቃሚውን በማይጎዳ መንገድ ቀስ በቀስ ከድጎማ ለመውጣት የሚያስችል የዋጋ ግንባታ በማድረግ የተሰብሳቢ ሂሳብ ጭማሪው በነበረው የጭማሬ ፍጥነት እንዳይቀጥል ተደርጓል። Ø ነገር ግን የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ የነበሩ ችግሮች አሁንም ድረስ ሳይፈቱ፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች እየተፈጠሩ ዘርፉን ውስብስብ እያደረጉት ይገኛል፤ Ø የነዳጅ ግብይቱን ላይ ያለው ግልፅ ህገ-ወጥነት እና ሌብነት እየሰፋ በመምጣቱ የችግሩን ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር ጥናት ተደርጓል፤ በጥናቱ የተለዩ ችግሮች፡- - በህገ ወጥ መንገድ በመሸጥ የሚገኘው ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑ - የነዳጅ ኩባንያና ማደያ ያልተገባ ጥቅም መፈለግ እና ሃላፊነትን አለመወጣት - በሁሉም የተቆጣጣሪ አካላት የሚስተዋል ስነምግባር ጉድለት፥ አቅም ማነስ - በስራ ላይ ያለው የገበያ ድርሻ አሰራር ችግር - አቅርቦቱ ተገማች አለመሆን በየጊዜው መቆራረጥ የቁጥጥርና ክትትል ስራው በቴክኖሎጂ የተደገፈ አለመሆን እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች - ሕገወጥነትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የሕግ ማእቀፎችን ወደ ስራ ማስገባት - በግብይት ሰንሰለቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን ማድረግ እና ሕጋዊ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ - የቀጥታ ተጠቃሚ ድርጅቶችን የነዳጅ አጠቃቀም ጥናት ማድረግና ጥናቱ በተገኙ ግኝቶች መሠረት ማስተካከያ ሥራዎች የተሰሩ መሆናቸው - በሕገወጥ ሥራ ላይ ተሰማርተው የተገኙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እና - የአቅርቦት ስርዓቱ ግልጸኝነት እንዲኖረውና የቁጥጥር ሥራዎችን ማቅለል የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በማስለማት ወደ ስራ እኒዲገቡ ማድረግ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ |