የንግድ ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ ላይ የተቋማቱ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎል
|
የንግድ ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ ላይ የተቋማቱ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎል በጉበኤው ላይ የሚንስቴር መ/ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት የ2018ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቦ በመገምገም ላይ ይገኛል። ከቀረቡት ሪፖርቶች አንዱ የባለስልጣን መ/ቤቱ አፈፃፀም ሲሆን በቀረበው ሪፖርት በነዳጅ ግብይት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማጥራትና የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ጥናት በሩብ ዓመቱ ስለመከናወኑ የቀረበ ሲሆን በዚህም ችግሮችን የመለየት ሥራ ተሠርቷል ። በዚህም በጅቡቲ ወደብ ላይ የነዳጅ ስርጭት ችግሮች፣ ኩባኒያዎች ለማደያዎች በሚያቀርቡት ነዳጅ ፍትሀዊ አለመሆን፣በነዳጅ ማጓጓዝ ስራ ላይ ያሉ ችግሮች፣በማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ ችግር ፣የተቆጣጣሪ አካላት ችግሮች እና የነዳጅ አቅርቦት ተገማች አለመሆን በጥናቱ ተለይተው ቀርበዋል። ሕግ በማስከበር ሂደት 214,358 ሊትር ነዳጅ የተወረሰ ሲሆን በሕገወጥ ሥራ ላይ ተሰማርተው የተገኙ 66 ሰዎች ክስ እንደተመሰረተባቸው በሪፖርቱ ቀርቦል። |