ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት

 

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ

በአዲሱ ዓመት መባቻ የበርካታ ዓመት ቁጭት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁ እና በመስከረም ወር መባቻ የከርሰ ምድር ሀብታችን የሆነው የተፈጥሮ ጋዝ መውጣቱ የኢትዮጵያ እድገት መልህቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን የሚጠግን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች ውጤት እያስገኙ እንደሚገኙም አመልክተዋል።

ከነጠላ ወደ ብዝሃነት የኢኮኖሚ ልማት በመሸጋገር እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች የኢትዮጵያ ኤክስፖርት እያደገ እና ኢኮኖሚው ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ ይገኛል ብለዋል።

የህዝቡን ኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት የታዳሽ ኃይል መሠረተ ልማት በቀጣይ ዓመታት በበቂ እንደሚገነባ፣ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲስፋፋና ተደራሽ እንዲሆን እንደሚደረግ እና ለኤክስፖርት ንግድ የሚበቃ የኤሌክትሪክ አቅርቦት በማሣደግ ለቀጠናዊ ኢኮኖሚ ትስስር መሠረት እንደሚጣል ጠቅሰዋል፡፡