ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክትን አስመረቀች፡፡

 

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክትን አስመረቀች፡፡

መስከረም 22/2018 (ነ.ኢ.ባ)

በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) መርቀው ያስጀመሩ ሲሆን በተመሳሳይም በዓመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር ማምረት አቅም የሚኖረው ሁለተኛው ዙር ሥራም አስጀምረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ ሳይሆን ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነ ግብዓት ማቅረቢያም ጭምር ሲሆን ይህ ደግሞ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም ለሃይል ማመንጫ እና ለክሪፕቶ ማይኒንግ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን የሚያቀርብ እንደሆነም ተነግሯል፡፡