የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

 

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

አዲስ አበባ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በዘርፉ በ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ።

በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛው ሩብ ዓመት በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎች በተመለከተ ዋና ዋና የትኩረት መስኳች ላይ የነበሩ አፈፃፀሞች ላይ የታዩ ጥንካሬዎች እና በክፍተት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ዳካማ ጎኖችን ለማረም አላማ ያደረገ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በንግግራቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ሀገር አቀፍ የንግድ ምዝገባና ኢንስፔክሽን አፈፃፀም ፣የውጭ ንግድ አፈፃፀም ከፍተኛ መሆን ፣2ኛው የንግድ ሳምንት ኤግዝቢሺንና ባዛር ከባለፈው ዓመት የንግድ ሳምንት ለየት ባለ ጥራት የተዘጋጀና ልምድ የተቀመረበት መሆኑ እንዲሁም የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር በተሳካ ሁኔታ የተካሄደበት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ንግድ የተጀመረበት መሆኑን በጥንካሬ የተነሱ ነጥቦች ነበሩ። በሌላ በኩል በሩብ ዓመቱ በጥራት መንደር የሚሰጡ የወጪና ገቢ ምርቶች ፍተሻ እንዲሁም የገበያና ፋብሪካ ምርቶች ኢንስፔክሽን የተሻለ ስራዎች የተከናወኑ ቢሆንም በላብራቶሪና ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ክትትል ላይ ክፍተቶች መስተዋላቸውን ገልጸዋል።
 

የንግድ ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ ላይ የተቋማቱ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎል

 

የንግድ ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ ላይ የተቋማቱ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎል 

በጉበኤው ላይ የሚንስቴር መ/ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት የ2018ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቦ በመገምገም ላይ ይገኛል። ከቀረቡት ሪፖርቶች አንዱ የባለስልጣን መ/ቤቱ አፈፃፀም ሲሆን በቀረበው ሪፖርት በነዳጅ ግብይት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማጥራትና የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ጥናት በሩብ ዓመቱ ስለመከናወኑ የቀረበ ሲሆን በዚህም ችግሮችን የመለየት ሥራ ተሠርቷል ። በዚህም በጅቡቲ ወደብ ላይ የነዳጅ ስርጭት ችግሮች፣ ኩባኒያዎች ለማደያዎች በሚያቀርቡት ነዳጅ ፍትሀዊ አለመሆን፣በነዳጅ ማጓጓዝ ስራ ላይ ያሉ ችግሮች፣በማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ ችግር ፣የተቆጣጣሪ አካላት ችግሮች እና የነዳጅ አቅርቦት ተገማች አለመሆን በጥናቱ ተለይተው ቀርበዋል። ሕግ በማስከበር ሂደት 214,358 ሊትር ነዳጅ የተወረሰ ሲሆን በሕገወጥ ሥራ ላይ ተሰማርተው የተገኙ 66 ሰዎች ክስ እንደተመሰረተባቸው በሪፖርቱ ቀርቦል።

 

የሀገርን ጥቅም በማስቀደም ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር

 

የሀገርን ጥቅም በማስቀደም ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር

ሀገራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያ ቁመና በሚል ርዕስ በወቅታዊና ሀገራዊ ቀዳሚ አጀንዳ ላይ የተቋሙ ሠራተኞች ውይይት አደረጉ፡፡

ውይይቱን በንግግር ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) አፅኖት ሰጥተው እንደገለጹት ከየትኛውም የውስጥ አጀንዳችን በላይ በብሔራዊ አንድነታችን እና ጥቅማችን ዙሪያ የጋራ እና የጸና አቋም ሊኖረን ይገባል ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ሠራተኞችም ብሔራዊ አንድነትን ማስቀደምና የመጡ ለውጦችን ለማስቀጠል ተቋማዊ አሰራሮችን ማሻሻል እንደሚያስፈልግና በኢትዮጵያ አንድነትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አንድ አቋም መያዝ እንዳለበት የጋራ አቋማቸውን ገልፀዋል፡፡
 

Authority Recognized for its Contribution to the pre- 2nd Africa Climate Change Conference Exhibition

 

Authority Recognized for its Contribution to the pre- 2nd Africa Climate Change Conference Exhibition

The Authority was honored with a certificate of recognition for its contributions to the 2nd Africa Climate Change Conference. The acknowledgment program was organized by the Ministry of Water and Energy in conjunction with the Energy Expo held prior to the conference.

Zewge Worku, the Lead Executive Engineer for Energy Efficiency and Conservation, accepted the certificate on behalf of the Authority during a ceremony attended by key stakeholders. Dr. Engineer Sultan Wali, the State Minister for Energy Sector Development at the Ministry of Water and Energy, presented the certificates to all recipients, celebrating their vital roles in the event.

 

የኢነርጂ ብቃትና ቁጠባ ውጤታማነትን መገምገምና ማረጋገጥ

  የኢነርጂ ብቃትና ቁጠባ ውጤታማነትን መገምገምና ማረጋገጥ ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ተግባርና ሀላፊነቶች መካከል አንዱ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ መሠረት ባለስልጣን መ/ቤቱ በተለያዩ ኢንዲስትሪዎች ላይ ቀደም ሲል በኢነርጂ ኦዲት ኩባኒያዎች የተሰሩ ኢነርጂ ኦዲት ስራዎችና በኦዲት ጊዜ የተለዩትን የኢነርጂ መቆጠቢያ መንገዶች (Energy Conservation Measures) ተግባራዊ መደረጋቸውን ወይም ማስተካከያ መወሰዱንና በማስተካከያው መሰረት የተቆጠበውን ኢነርጂ የመለካት እና የማረጋገጥ ስራ እየሰራ ይገኛል። በዚህም ባሳለፍነው ሣምንት በስድስት ኢንዱስትሪዎች ላይ ስራው ተከናውኗል፡፡  

Page 2 of 4