የኢነርጂ ብቃትና ቁጠባ ውጤታማነትን መገምገምና ማረጋገጥ

  የኢነርጂ ብቃትና ቁጠባ ውጤታማነትን መገምገምና ማረጋገጥ ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ተግባርና ሀላፊነቶች መካከል አንዱ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ መሠረት ባለስልጣን መ/ቤቱ በተለያዩ ኢንዲስትሪዎች ላይ ቀደም ሲል በኢነርጂ ኦዲት ኩባኒያዎች የተሰሩ ኢነርጂ ኦዲት ስራዎችና በኦዲት ጊዜ የተለዩትን የኢነርጂ መቆጠቢያ መንገዶች (Energy Conservation Measures) ተግባራዊ መደረጋቸውን ወይም ማስተካከያ መወሰዱንና በማስተካከያው መሰረት የተቆጠበውን ኢነርጂ የመለካት እና የማረጋገጥ ስራ እየሰራ ይገኛል። በዚህም ባሳለፍነው ሣምንት በስድስት ኢንዱስትሪዎች ላይ ስራው ተከናውኗል፡፡