የነዳጅ ግብይት ዘርፍ

 

የነዳጅ ግብይት ዘርፍ

  • የነዳጅ ግብይት ዘርፍ ስንል የታችኛው የግብይት ሰንሰለት ወይም downstream sector ሲሆን የነዳጅ ውጤቶች ፍላጋና ማምረትን አያካትትም፡፡
  • ይህ የግብይት ሥርዓት ነዳጅን ከውጭ በመግዛት ማቅረብን፣ የጥራት ቁጥጥርን፣ በጅምላና በችርቻሮ ማከፋፈልን፣ ነዳጅ ማጓጓዝንና ማከማቸትን እንዲሁም የትርፍ ህዳግ ፣የታሪፍና የዋጋ ግንባታ አሠራርን፤ የግብይት ተዋናዮች የፈቃድ አሠጣጥን፣ በግብይቱ ተዋንያኖች መካከል የሚኖረው የግንኙነት አግባብ የሚመራበት የተገደበ የግብይት ሥርዓትን ያጠቃልላል፡፡
  • ከዚህ በተጨማሪ በግብይት ሰንሰለቱ ተሣትፎ ያላቸው የቁጥጥር አካላት ሚና በግልፅና በዝርዝር የሚገለፅበትና ሥልጣንና ኃላፊነታቸውን በትክክል ስለመወጣታቸው ክትትል የሚደረግበት አግባብ የሚወሰንበት ሥርዓት ነው፡፡